ዝናውን ሰምቼ ፈለኩት ከሾላ ላይ ሆኜ አየሁት ከአንተ ጋር ነኝ አለኝ መድኀኒቴ ዛሬስ መዳን ሆነልኝ ለቤቴ የረከሰው ቤቴን ጌታዬ ሳይንቀው ጨለማውን ገፍ ብርሃን አደረገው ለገናና ክብሩ ለእርሱ ተንበርክኬ ዛሬ ተለወጠ ጎስቋላ ህይወቴ አዝ___ እንደምን ወደደኝ ምን አግኝቶ ከኔ ህይወቴ ያደፈ ነው የገባውን ኩነኔ አርኩ ግን ጎበኘኝ በማዳን አዋጁአ ስሙን አተመብኝ አደረገኝ ልጁ አዝ__ የአብርሃም አምላክ የእስራኤል መና የጠፋውን ሊፈልግ ሊያደን መጥቷልና እኔም ጎበኘኝ በማዳኑ ጥሪ ወሮታውን ክፈይ ነፍሴ ሆይ ዘምሪ
September 1, 2026 56