📝ኤጀንሲው የ2017 ዓ.ም የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃጸም ገመገመ!!
ምገባ ኤጀንሲ -ሚያዚያ 3/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ የ2017 በጀት ዓመት የተቋሙን የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃጸም የኤጀንሲው አመራርሮች፣ አጠቃላይ ሰራተኞች በተገኙበት በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጧል።
ሪፓርቱን ያቀረቡት የተቋሙ እቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዮሃንስ ገ/ፃድቅ ኤጀንሲው በዘጠኝ ወር የሰራቸውን ዝርዝር ተግባራት በሰነድ በተደገፈ ሪፓርት አቅርበዋል።
በግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሽታዬ መሃመድ ተቋሙ ሰው ተኮር ተግባራት ላይ ፣ የዕለት ጉርስ ያጡ ዜጎችን በቀን አንድ ጊዜ በተስፋ ብረሃን የምገባ ማዕከላት መመገብ፣በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተማ ውስጥ በሚገኙ በመንግሰት ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ(ቁርስና ምሳ) ምገባ አገልግሎት እንዲሁም የትምህርት ግበዓት አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀው የቀረበው ሪፓርት የተሻለ አፈፃፅም የታየበት መሆኑንና በቀሩት ሶስት ወራት በልዩ ሁኔታ ሁሉም የተቋሙ ሰራተኞች ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አሳስበዋል።
በመድረኩ የኤጀንሲው ሰራተኞች በበኩላቸው የቀረበው ሪፓርት የተሻለ መሆኑን አንስተው በጥንካሬ የታዩ ስራዎችን በማስቀጠል ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ ወራት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ጠንክረው እንደሚሰሩ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በመጨረሻም በኤጀንሲው ሰራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በኤጀንሲው አመራሮች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
ማሳሰቢያ :- ውድ የኤጀንሲው ሰራተኞች እና ማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች በቅድሚያ ለምታደርጉልን አስተያየትና ጥቆማ እያመሰገን ከዛሬ ጀምሮ ከታች በተቀመጠላችህ ማስፈንጠሪያ/link አድሱን የኤጀንሲው ማህበራዊ ድረ ገፅ እየገባችሁ የቀደመ ሚናችሁን እንድትወጡ ስንል እናሳስባለን።
https://www.facebook.com/61575251932855/posts/122094478412841731/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v
https://t.me/feedingagency8
https://youtube.com/@addisababacityadminstrationfa?si=QyoZiayxIloRxa5j
"ከነዋሪዎች እፎይታ እስከ ብቁ ትውልድ ግንባታ"!!
Facebook
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ
📝የኤጀንሲው የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ተመዘነ!!
ምገባ ኤጀንሲ :- መጋቢት 30/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስ ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ፣የፕላንና ልማት ኮሚሽን እና የከንቲባ ጽ/ቤት በጋራ በመሆን በምገባ ኤጀንሲ በመገኘት የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት...

April 12, 2025 1.1K