በደረሰዉ ድንገተኛ ቃጠሎ ምክንያት ሆስፒታሉ ሙሉ በሙሉ ስራ አቁሟል " - የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ➡ "… — Ehealth — TG.ME

Forwarded fromTITIKVAH-ETHIOPIA
" በደረሰዉ ድንገተኛ ቃጠሎ ምክንያት ሆስፒታሉ ሙሉ በሙሉ ስራ አቁሟል " - የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ

" የጤና ባለሙያዎች እና የአከባቢው ነዋሪዎች ተረባርበዉ ተኝተዉ የሚታከሙትንና በፅኑ ሕሙማን ክፍል የነበሩትን ማትረፍ ችለዋል!! "

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዛሬ ከባድ የእሳት አደጋ እንዳጋጠመውና በቃጠሎው ምክንያት የሆስፒታሉ ዋናው የአገልግሎት ሕንፃ ሙሉ በሙሉ በመውደሙ ሆስፒታሉ አገልግሎት ማቆሙን የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ኤካ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የሆስፒታሉ ዋና ዋና ሕክምናዎችና የላብራቶሪ ስራዎች ይከናወኑበት የነበረዉ ይህ G+1 ሕንፃ ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረና የቀዶ ሕክምናን ጨምሮ ተኝተዉ የሚታከሙና የፅኑ ሕሙማን ክፍሎችን የያዘ የሆስፒታሉ ዋነኛ ሕንፃ እንደነበር ገልጸዋል።

ይኸው ሕንፃ ከቀኑ 8:30 አከባቢ ጀምሮ ለጊዜው መንስኤው ባልታወቀ የእሳት አደጋ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት አስታውቀዋል።

የጤና ባለሙያዎችና የአከባቢው ነዋሪዎች በመረባረብ ተኝተዉ የሚታከሙትንና በፅኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ የነበሩ ታካሚዎችን ማትረፋቸዉን የገለፁት አቶ ፀጋዬ ቁጥርና ሁኔታዉ በደንብ የሚጣራ ቢሆንም የሆስፒታሉ ትልልቅ የሕክምና መሳሪያዎችም ጉዳት ማስተናገዳቸውን ገልፀዋል።

ይህ ቃለ ምልልስ በተካሄደበትም ሰዓት በሁለት የእሳት ማጥፊያ መኪኖች ታግዞ የእሳት ማጥፋት ርብርቡ የቀጠለ ሲሆን እሳቱ ሙሉ በሙሉ አለመጥፋቱን አቶ ፀጋዬ ኤካ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
👎1
July 26, 2025 81