Hanif Multimedia - ሐኒፍ መልቲሚዲያ: post #3161 — TG.ME

በአፋር ክልል ወረር ከተማ የሚገኘው መርከዝ ሰላም በትላንትናው ዕለት 36 የሚሆኑ የቁርአን ሂፍዝ ተማሪዎችን ለ6ኛ ጊዜ አስመርቋል። በዕለቱም የክልሉ የመጅሊስ አመራሮች ፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።

ቀደም ሲል ለመርከዙ ተማሪዎች በሐኒፍ ኢስላማዊ ድርጅት አዘጋጅነት ለ 4 ጊዜያት በተለያዩ የዒልም ዘርፎች ላይ አጫጭር ኮርሶች ሲሰጣቸው የቆየ ሲሆን። በዚሁ ልዩ አጋጣሚ ሐኒፍ ኢስላማዊ ድርጅት የተሰማውን ደስታ እየገለፀ ፤ ለተመራቂ ተማሪዎች ፣ ወላጆችና የመርከዙ አስተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ይወዳል።

ለዚህ ውጤት የለፉትን የመርከዙ ኃላፊዎችና አስተማሪዎችና አጋሮች በሙሉ አላህ ልፋታቸውን ይቀበላቸው በኸይርም ይመንዳቸው ፤ ተመራቂ ተማሪዎችንም ባወቁት የቁርአን ፋና ሰሪና ለሌሎችም አስተማሪ በመሆን ይህን ኸይር የሚያስቀጥሉ ያድርጋቸው።

Hanif Islamic Organization ∣ مؤسسة حنيف الإسلامية

@HanifMultimedia
❤7👍5👏2
August 3, 2026 2.1K 2