ማነው ደሞ «ደም ምለሳ»ን ኋላ ቀር ባሕል ያደረገው? አባቴ ደምመላሽ ባይኖር ጥጋበኛው ሁሉ እየተነሳ ማንንም… — Tamene Mengste Wube — TG.ME

ማነው ደሞ «ደም ምለሳ»ን ኋላ ቀር ባሕል ያደረገው?

አባቴ ደምመላሽ ባይኖር ጥጋበኛው ሁሉ እየተነሳ ማንንም ይቀትል ነበር።

ደግሞስ የጎጃሙን ጀግና በላይ ዘለቀ ላቀውን «የኢትዮጵያ ደም መላሽ!» የምንለው በዚህ የጀግና ግብሩ አደለም እንዴ?

ባይዜ ራሡ በላያ እና ወንድሙ እጅጉ ዘለቀ ወደ ጫካ የወጡበት የመጀመሪያ ምክኒያት የአባታቸውን ደም ለመመለስ ነበር።

የባሰ ጠላት አገኙ፤ፋነኑ።

ምን ለማለት ዩ🥰

ሕግ እና ሥርዓት በተመናመነበት እንደ ኢትዮጵያ ባለ አገር ወንድ ልጅ የወንድሙን ደም የሚመልስ ባይሆን ኖሮ ተከባብረን አንቀጥልም ነበር።

በፖለቲካ ፓወር ባለንስ የሚባል እንዲህ ያለው ነገር መሰለኝ።

ሂድ መካከለኛው ምሥራቅ...

እሥራኤል አንድ ዜጋዋ ሲነካ ተጣድፋ ደሙን ትመልሳለች።ኢራንም እንዲሁ ናት።አሜሪካ ራሧ!

ዌል እንግዲክ🤫

ደም የሚያደርቅ አያት ያለኝ ሰው ነኝ።ማስታረቁን እናውቅበታለን።ሆኖም የገዳይ ወገኖች ለመታረቅ ራሡ ደም መላሽ ወንድም እንዳለህ ማወቅ አለባቸው።

ምን ለማለት ነው?

«ደምመላሽ ተብዬ
ሥም ወቶልኝ ነበር»

ያለውን ዘፋኝ ሙዚቃውን እንዲያርም ንገሩት።

ሥሙንም መሥፍን ከማለት ወደ ደምመላሽነት ይመልሰው።

ይሄው ነው🙁
❤1👏1
August 30, 2026 183 2