የእኛ ትውልድ ከብዙ ትግል በኋላ ወደ ማንነቱ ለመመለስ መንገድ ላይ ይገኛል።የትውልድ ቀዬውን፣ወላጆቹን፣ማንነቱን መውደድ ጀምሯል።
በታንጎ እና ማሪንጌ ከመደነስ ወደ እስክስታ እና ዋንጫ ልቅለቃ፣ከውቤ በረሃ እና ቺቺኒያ ናይት ክለቦች ወደ ሻደይ፣አሸንዳ፣እንግጫ ነቀላ፣ጥምቀት፣ፉከራ፣ቅራርቶ እና የመሳሰሉ አገር በቀል መድረኮች ተመልሷል።
ከቤል ሱሪ ወደ ተነፋነፍ፣ቂጥ አጉልቶ ከሚያሳይ የሴት ልብስ ወደ ውብ የአገር ባሕል ቀሚስ ተዛውረናል።
ከ90ዎቹ እኛን የማይመሥሉ ፊልሞች ወደ ድለቃ እና የገጠር ድራማዎች አድገናል።
ትውልዱ ተገዶም ሆነ ወዶ በጎጃም፣ጎንደር፣ወሎ፣ሸዋ፣ሐረርጌ፣ጋሞጎፋ ገጠሮች ሄዶ ወደመኖር ተሸጋግሯል።
ይሄ እጅግ በጣም ደስ የሚል ለውጥ ነው።
ሆኖም ዛሬም ቢሆን ነባር እውቀቶች በንባብ፣በቃላዊ የእውቀት ሽግግሮች፣በግጥም እና በማኅበረሰብ ዜማዎች ተቀማጥለው ሲቀርቡ ዓላይም።
ውብ ሴቶቻችን ስክሪን ላይ እየመጡ ከዓመታት በፊት በተዜሙ ሙዚቃዎች ከመወዝወዝ ያለፈ ፈጠራ ዕያሳዩን አይደለም።
የባሕል ሙዚቃዎቻችን ቪዲዮዋቸው ሲያምር ታሪክ እያበላሹ፣ግጥማቸው ልል እየሆነ፣አዚያዚያማቸው ለልብ አልሞላ እያለ ተቸግረናል።
ታነስ አነስ...
ፍቅርዓዲስ ነቅዓጥበብ እና ይሁኔ በላይ የተባሉ ውዶቻችን ለመጨረሻ ጊዜ ያወጧቸው አልበሞች የነሱ አልመሥለኝ እስኪሉ ድረስ ሳስተው አግኝቻቸው አለሁ።
የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾች የኪነጥበብ ሰዎችን ትኩረት መቀማታቸው ለዚህ ዋናው ተጠያቂ ይመሥለኛል።
ይህ ግን ለእኛ ገና በ18ኛው የዘመን ክፍል የዓለም ሥልጣኔ ደረጃ ላለን ኋላቀሮች ተገቢ አደለም።
ልቦለድ ከጀመርን ገና መቶ ዓመታችን ነው።የተደራጀ ሙዚቃ ከጀመርን 50 ዓመታችን ነው።ፊልማችን ከ30 ዓመት የበለጠ ዕድሜ የለውም።ቴአትራችን ገና ልጅ ነው።
ወዘተ ወዘተ
እናም ፈጠራ ላይ እንበርታ🥰

3August 28, 2026 221 2