ኦሮሞ ከአዶናይ ብርሃነ በጣም የላቀ የባሕል አምባሳደር አለው።
አርፏል።
ሥሙ ተስፋዬ ገብረአብ ይባላል።
ለኦሮሞ ሕዝብ ያለውን ፍቅር ያልገለጸባቸው መጽሐፍቱ ጥቂት ናቸው።
ተስፋዬ በአደኣ ገጠሮች፣በጋራበሩ ኮረብታዎች፣በቢሾፍቱ ሐይቅ ዳርቻ አብሯቸው እንደኖረ ሥለሚናገርላቸው ኦሮሞዎች ሲጽፍ በፍቅር ያነሆልላል።
የኦሮሞ ልሂቃንም ይሄንን ውለታው አስልተው «ገዳ(?)» ብለውታል።
ከባድ ማዕረግ ነው።
ኦሮሞ ከተስፋዬም በላይ ሌላ የላቀ አምባሳደር አሉት።ፕሮፌሠር አሥመሮም ለገሰ ናቸው።
ወደ ጥንት የኦሮሞ መሠረት—ቦረና ወርደው ከአርብቶ አደሩ ጋር ኖረው ነው—ባሕሉን እና የገዳ ሥርዓቱን አጥንተው ለዓለም ያሳወቁት።
እኔ ራሴ በእሳቸው ጥናት ላይ የተመሠረተውን የኦሮሞ ታሪክ ሳይሆን ይቀራል የተማርኩት?
በዚያም ምክኒያት የኦሮሞ ሕዝብ ይደላኛል።
አዶኒ ግን በእነ ጸገመ፣በእነ በዓሉ ግርማ፣በእነ ሰለሞን ዴሬሳ ደረጃ ሊወከል የሚገባውን ኦሮሞ ወክሎ አምባሳደር መሆን የሚችል አይመሥለኝም።
ሚሊዮን ማስከተል ሌላ፤ምልዑ አርኣያ መሆን ሌላ።
ከሁሉ በፊት ያንብብ፣ይወቅ፣ይጻፍ—ይዘት—የሚባለውን ነገር የሚያሟላ ሥራ ይከውን።
በመርሕ ደረጃ የአዶናይ ደጋፊ ነኝ።ግን እውቀቱ፣ጥልቀቱ እና ችሎታው ላይ ባለፈው ሕዳር ያነሳሁትን ጥያቄ አልመለሰልኝም።
በውነቱ tt ላይ ይዘቱ ሲመጣልኝ ለመመልከት አመነታለሁ🙁

August 27, 2026 243 1