«ቀይ ባሕር ሲቀላ» ሥለ ሰሜን ካነበብኳቸው የቅርብ ጊዜ መጽሐፍት መካከል ምናልባትም ሁለተኛው ጣፋጭ መጽሐፍ ነው።«አውሮራ»ን ስለደገምኩት እሱ ቀዳሚ ሆኖ ማለት ዩ።
«ቀይ ባሕር ሲቀላ» ውስጥ ሥለ ምጽዋ የተጻፈው ሁሉ በአግራሞት ሲያተራምሰኝ ነበር።
ምጽዋ የባሕር ዳርቻ ከተማ ናት።ሞቃታማ ከተማም ናት።
እናም ሰዎች በዚያ ነፃ ናቸው።
እንዲህ ያለ ከተማ ነው—እኔን የሚደላኝ።
ጄጅ—የሚያረገኝ ሰው የሚበዛበት ቦታ መገኘት አልወድም።የራሴ የአመጋገብ፣አለባበስ፣አነጋገር፣አጻጻፍ፣አኗኗር ዘዴ አለኝ።
በቃ አለኝ።
ግን የመሐል አገሩ እና የእኔ ዐይነቱ ሰው ፕሮቶኮል ያበዛል።ሥለሆነም ያስጨንቀኛል።
በዚህ ምክኒያት ነው—ድግስ የማይመቸኝ።
ሥለ ድግስ መጻፍ ወይም ማውራት እንጅ መሳተፍ አልወድም።ወደ ዘመድ ቤት መሔድም ምቾት አይሰጠኝም።
«ብላ» ይሉኝ'ና አበላሌን ይገመግማሉ።
ኤጭ😥
እናም እንደ ምጽዋ፣ሎግያ፣ሰመራ፣ወንጂ፣አዳማ ወዘተ ያሉ ሰው ለቀቅ ብሎ ሳይገማገም የሚኖርባቸው ከተሞች የነፍሴ ፍሥሐ የሚቀዳባቸው ይመሥሉኛል።
«ቀይ ባሕር ሲቀላ» ውስጥ ያዬኋት ባጽዕ(?) እንዲያ ናት።
ፍርድአወቀ ማሞ ሲነግሩንኮ «ምጽዋ ባል እና ሚስት በረንዳ እና የእግረኛ መንገድ ላይ አልጋቸውን አውጥተው፣ተቃቅፈው የሚተኙባት ከተማ ናት፤»
ደሞ ምጽዋ—ፊያሜታ ጊላይ እና ጸጋዬ ኃይለማርያም ለዋው ፍቅራቸው የተገናኙባት ከተማ ናት።
ፊያሜታ ያን'ለት ቀዩን ባሕር ከአድማስ ባሻገር ድረስ ዕያዬች ከራሷ ጋር ስትጫወት ነው—ጸጋዬ ያገኛት።ውብ ነጠላ ለብሳ «ነጭ እርግብ ትመሥል ነበር» ብሎናል—ደራሲው።
ያች ምጽዋ ትናፍቀኛለች።
«የማያውቁት አገር አይናፍቅም፤» ያለ ማነው?
ጭዌው የኢማጂኔሽን ልዩነት ነው—ብሮ።
ጎንደርን ሳላያት ትናፍቀኝ ነበር።
ሜይ ቢ አለማወቅ—አለማንበብ፣ሙዚቃ ላይ አለመሥማት ምናምን ተሆነ እሺ

August 27, 2026 210