G-Tutorialclass: post #5245 — TG.ME

በ148 ቀበሌዎች ዝናብ የለም‼️

በትግራይ ክልል በድርቅና በወታደራዊ ምልመላ ምክንያት ህዝቡ ለእንግልት መዳረጉ ተነግሯል።

​የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል በሚገኙ 148 ቀበሌዎች ላይ አንዲት ጠብታ ዝናብ እንኳ አልዘነበም ብሏል።

በ​ድርቁ በሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳት እያለቁ ሲሆን፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖች ደግሞ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ይፈልጋቸዋል ተብሏል።እርዳታ እንደምንም ቢገባም "ለታጣቂ ይሰጣል" የሚል ስጋት በረጅዎች ዘንድ መኖሩ ተጠቁሟል።

​ ህወሓት ወጣቶችን በማፈስ ወደ ጦርነት እያሰማራ ይገኛል መባሉን ተከትሎ፣ የትግራይ ህዝብ በአንድ በኩል በረሃብና በድርቅ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በጦርነትና የልጆቹን ህይወት በማጣት እጥፍ ድርብ ስቃይ እየደረሰበት መሆኑ ዘገባው አመልክቷል።
አዩ
=====================
💎👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
@GTutorialclass
🤯1
August 16, 2026 84 1