በ148 ቀበሌዎች ዝናብ የለም‼️
በትግራይ ክልል በድርቅና በወታደራዊ ምልመላ ምክንያት ህዝቡ ለእንግልት መዳረጉ ተነግሯል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል በሚገኙ 148 ቀበሌዎች ላይ አንዲት ጠብታ ዝናብ እንኳ አልዘነበም ብሏል።
በድርቁ በሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳት እያለቁ ሲሆን፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖች ደግሞ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ይፈልጋቸዋል ተብሏል።እርዳታ እንደምንም ቢገባም "ለታጣቂ ይሰጣል" የሚል ስጋት በረጅዎች ዘንድ መኖሩ ተጠቁሟል።
ህወሓት ወጣቶችን በማፈስ ወደ ጦርነት እያሰማራ ይገኛል መባሉን ተከትሎ፣ የትግራይ ህዝብ በአንድ በኩል በረሃብና በድርቅ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በጦርነትና የልጆቹን ህይወት በማጣት እጥፍ ድርብ ስቃይ እየደረሰበት መሆኑ ዘገባው አመልክቷል።
አዩ
=====================
💎⬇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
@GTutorialclass
1August 16, 2026 87 1 1

