የፖለቲካ እስረኞችን ከማይካድራ ጭፍጨፋ ፍርደኞች ጋር በይቅርታ አንድ ላይ ለመፍታት መታቀዱ ተቃውሞ አስነሳ‼️
በአማራ ክልል ከተቀሰቀሰው ግጭት ጋር በተያያዘ በማረሚያ ቤቶች ተይዘው የሚገኙ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ከመንግስት የቀረበላቸውን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም በማለት ጠንካራ ተቃውሞ ማቅረባቸውን መዘገቡ ይታወሳል።
መንግስት የፖለቲካ ታሳሪዎቹን ከስድስት ዓመታት በፊት በማይካድራ ከተፈፀመው ዘግናኝ የጅምላ ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ "በሰብአዊ ፍጡር ላይ የሚፈፀም ወንጀል ተከሰሱ እና ከተፈረደባቸው አካላት ጋር በአንድ ላይ አደባልቆ በይቅርታ ለመፍታት ማቀዱ ታሳሪዎቹን አስቆጥቷል።
የመረጃ ምንጮች እንደገለጹት የፖለቲካ እስረኞቹ ይህንን ውሳኔ "እጅግ ዘግናኝ የሆነ ግድያና ጭፍጨፋ ፈጽመው ፍርድ ካገኙ ግለሰቦች ጋር እኩል በማሰለፍ በሕዝብ ዘንድ በተመሳሳይ እይታ እንዲታዩና የወንጀሉ ተካፋይ ተደርገው እንዲሳሉ ሆን ተብሎ የተሸረበ ሴራ ነው" ሲሉ አውግዘዉታል።
ታሳሪዎቹ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ይህንን የይቅርታ ሀሳብ አዘጋጅቶ ለመንግስት ማቅረቡን በመግለጽ የኮሚሽኑ እርምጃ እጅግ እንዳዘናቸውና ተስፋ እንዳስቆረጣቸው ተናግረዋል።
መንግስት በሚመጣው አዲስ ዓመት ከ1,300 በላይ ሰዎችን በይቅርታ ለማስፈታት አቅዶ የይቅርታ ደብዳቤ እያስፈረመ ይገኛል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ በርካቶች የቀረበላቸውን አነጋጋሪ የይቅርታ ሰነድ ቢፈርሙም 30 የሚሆኑ ታዋቂ የፖለቲካ እስረኞች ግን "አልፈርምም" በማለት አቋም ይዘዋል።
የቀረበው የይቅርታ ሰነድ አወዛጋቢ ቃል የሚከተለውን ያካትታል፦ «በአማራ ክልል ፅንፈኛው ቡድን በሚያደርገው ትግል ላይ መሳተፌ ስህተት መሆኑን በማመን መንግስትንና ሕዝብን ይቅርታ እጠይቃለሁ።
@gtutorialclass

1August 16, 2026 76 1