G-Tutorialclass: post #5239 — TG.ME

ድርቅ‼️
በሰሜን ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው ከባድ የድርቅ አደጋ ምክንያት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የቤት እንስሳት እያለቁ መሆናቸውን ከየአካባቢው የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል።
በትግራይ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች፣ በአማራ ክልል ዋግምራ ዞን፣ በሰሜን ጎንደር ጠለምትና የበየዳ ቆላማ አካባቢዎች የክረምት ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት የቁም እንስሳት እልቂት ይበልጥ እየከፋ መጥቷል።
በተለይም በሰሜን ጎንደር ጠለምት ቀጠና ከአስራ አንድ ሺህ (11,000) በላይ የቀንድና የጋማ ከብቶች እንዲሁም የበግና ፍየሎች ማለቃቸው ታውቋል።
በሌላ በኩል በትግራይ ክልል በአብዛኞቹ አካባቢዎች በዚህ ክረምት የተዘራና የበቀለ እህል ጨርሶ አለመኖሩን የአዩዘሀበሻ የመረጃ ምንጮቻች ገልጸዋል።
የድርቁ ስፋትና የሚያሳድረው ተፅዕኖ በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ከፍተኛ እየሆነ የመጣ ሲሆን፣ ሁኔታው እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የደረሱን መረጃዎች ያመላክታሉ።
👉ምስሉ ጠለምት ከሚገኙ የአዩዘሀበሻ ቤተሰቦች የተላከ ነው።
👉ሼር በማድረግ የሰብዓዊነት ግዴችሁን ተወጡ
(አዩዘሀበሻ)
=====================
💎👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
@Gtutorialclass
😢2🤔1
August 13, 2026 82 1