ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉ የ11 የሥራና ተግባር ትምህርት የሙያ አይነቶችን ዝርዝር አሳውቋል።
በአዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፓሊሲ ላይ "የሙያና ቴክኖሎጅ ትምህርት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ከእድሜያቸው ጋር የተመጣጠነ ሆኖ እንዲሰጥ ይደረጋል" በሚል አቅጣጫ መቀመጡን ያመለክታል።
በዚህ መሰረት በየደረጃው የሥራና ተግባር ትምህርት ከሌሎች ትምህርቶች ጋር ተቀናጅቶ እንዲሁም 7ኛ እና 8ኛ ክፍል ራሱን ችሎ ተማሪዎች በቀጣይ የሚፈልጉትን ሙያ እንዲመርጡ በሚያስችል መልኩ እየተሰጠ ይገኛል ብሏል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ደግሞ በሁለተኛው ዙር እንዲተገበሩ ለተለዩት 11 የሙያ አይነቶች ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል መርሐ ትምህርቶች እንዲሁም ለ11ኛ ክፍል የተማሪ ሞጁሎችና የመምህር መምሪያዎች ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል።
በመሆኑም እነዚህን ተጨማሪ የሙያ አይነቶች ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በ11ኛ ክፍል ለማስጀመር :-
• የክልሉ/የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ዝርዝር እቅድ በማዘጋጀት እና እቅዱን ለማከናወን በጀት በመያዝ የሙያ አይነቶችን በትምህርት ቤት እና በተማሪዎች ደረጃ በማስመረጥ፣
• የየሙያ አይነቱ መምህራንን በመቅጠር፣
• የመማሪያ ማስተማሪያ ግብዓት በሂደት በማሟላት፣
• መምህራንን እና የትምህርት አመራሮችን በማሰልጠን እና የህዝብ ንቅናቄ ስራዎችን በማከናወን ትምህርቱን ለማስጀመር ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።
ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉ የ11 የሙያ አይነቶችን ዝርዝር አሳውቋል።
@Gtutorialclass
2August 13, 2026 67

