#በአማራ ክልል የ2018 #የትምህርት ዘመን #የ8ኛ ክፍል #ክልላዊ ፈተና #ውጤት ይፋ ሆነ።
በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልል #አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።
ከሰኔ 3-5/2018ዓ.ም ለተከታታይ ሶስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት በቴክኖሎጅ ታርሞ ይፋ የተደረገ ሲሆን በክልሉ 173699 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸው ይታወቃል። ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች መካከልም 135003(77.72%)ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።
ተማሪዎችም ውጤታቸውን በሁለት አማራጮች ማየት የሚችሉ ሲሆን:-
🔴 በኮምፒውተር ወይም ስልካቸው ባለዉ የድር መፈለጊያ መተግበሪያ ( Web browser Application ) ላይ
1) ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara.ministry.et/#/result የሚለውን አድራሻ በመፃፍ
2) በሚመጣው ቅጽ (form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) እና ስም በአማርኛ በማስገባት
3) ዉጤት ይመልከቱ (Check your result) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማየት ይችላሉ፡፡
🔴 በተጨማሪም @emacs_ministry_result_qmt_bot በሚለው የቴሌግራም ቦት ላይ በመግባት ተማሪዎች ውጤታቸውን መመልከት የሚችሉ ሲሆን መጀመሪያ
1) start የሚለውን ይጫኑ!
2) በመቀጠልም ክፍልዎን ይምረጡ
3) ከዚያም ክልልዎን ይምረጡ
4) በመቀጠል የምዝገባ መለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስምን በማስገባት ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።
ተማሪዎች ማንኛውም ከውጤት ጋር የተያያዘ ቅሬታ ካላቸው ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ይችላሉ። ቅሬታቸውንም ለማቅረብ
🔴 በኮምፒውተር ወይም ስልካቸው ላይ ባለዉ የድር መፈለጊያ መተግበሪያ ( Web browser Application ) ላይ
1) ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara.ministry.et/#/complaint የሚለውን አድራሻ በመፃፍ
2) በሚመጣው ቅጽ(form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) እና የተማሪውን የመጀመሪያ ስም (First Name)በማስገባት
3) የትምህርት ዓይነት አሳይ(Fetch course) የሚለውን ቁልፍ በመጫን
4) ቅሬታ ማቅረብ የሚፈልጉበትን ይምረጡ
5) በመጨረሻም ሪፖርት (Add Complaint) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ።
🔵ማስታወሻ ፡ በቅድሚያ ቪፒኤን ማጥፋት ይኖርባችኋል፡፡
⚛ 2018ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል።
=====================
💎⬇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s

2August 2, 2026 124 1 1