FIT CORNER SPORT 🏅🏅🏅 ገቢዎች ሚኒስቴር ከጉሙሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የሰራተኞች ቀንን በድምቀት አከበረ።🏅🏅🏅 በቢሾፍቱ አየር ሀይል ማሰልጠኛ ጊቢ ውስጥ በተካሄደው መርሐግብር ላይ የኢፌዲሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳን ጨምሮ የገቢዎች ሚንስቴር ሚንስትር ኮምሽነር ዶ/ር ደበሌ ቃበታ እንዲሁም የጉሙሩክ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አዘዘው ጫኔ እና የየተቋማቱ ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል። ፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ በማለዳ አካላዊ እንቅስቃሴ በደማቅ ሁኔታ ያካሄደ ሲሆን ሩጫ፣የእግር ኳስ ውድድሮች እና ሌሎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችም የመርሐግብሩ አካላት ነበሩ። መሰል እንቅስቃሴዎች በሰራተኞች መካከል መካሄዳቸው ጤንነታቸውን ከመጠበቅ በተጨማሪም ማህበራዊ መስተጋብራቸውን ከፍ እንደሚያደርግ የፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንስትራክተር ነፃነት ካሣ ተናግረዋል። https://t.me/FitCorner https://www.tiktok.com/@netsisport?_r=1&_t=ZS-9657BjxWEZJ
July 29, 2026 538 1