♦️ ዘመናዊ ባርነት!!🚹🚺🚻
ጥንታዊ የባሪያ ንግድ የሚባለው በቆዳ ቀለሙ ጥቁር የሆነውን ሰው እንደ ከብትና የቤት እንስሳት ለገብያ አቅርቦ መሽጥ ነበር። ዛሬ ታላቋዋ አሜሪካ የምትባል አገር ታላቅ የሆነችው ከአፍሪካ እንደ ወርቅ፣ ቡናና ሌጦ በተሸጡ ጥቁር አፍሪካዊያን ባሮች ነበር። በአገራችንም እስክ ንጉስ ምንልክ/ሀይለስላሴ የነበረ ነው። ከዛ በዓለም አቀፍ ደረጃ በወንጀል ተፈርጆ ቀርቶል። "ኢትዮጵያን ዳግም ታላቅ እናደርጋታለን፤ ወደ ቀድሞ ከፍታ እንመልሳታለን" የሚለው የአብይ አገዛዝ ዘመናዊ ባርነት አንብሮል።
አንድ ተጋሩ ወዳጄ ከሳምንት በላይ ታስሮ መፈታቱን ነገረኝ። ምክንያቱን ስጠይቀው ያው ተጋሩ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ከሌሎች ጋር ታፍሶ ለግዳጅ ወታደራዊ እንደሆነ፤ ነገር ግን በተፈጥሮ አንካሳ በመሆኑ ለወታደርነት ብቁ እንዳለሆነ፤ ዝም ብሎ እንዳይለቁት ተጋሩ በመሆኑ ሰላሳ ሺ ብር ከፍሎ መውጣቱን ነገረኝ። አብሮ የታፈሱት አብዛኛዎቹ ኤርትራዊያንና ተጋሩ ስለሆኑ እስክ መቶ ሺ ብር እየከፈሉ ከእስር ቤት ውጥተዋል።
ወዳጄ በጣም የሚያሳዝነውና አንጀት የሚበሉት ከደቡብና ከኦሮሚያ የመጡ ልጆች ናቸው ይላል። አብዛኛዎቹ ሥራ ፍለጋ ደላላ ቤት ሄደው ነው። ለካ እያንዳንዱ ካብኔ አምስት አምስት ወጣቶች እንዲያመጡ ግዳጅ ተጥሎባቸዋል። እነሱም ደላላ ጠርተው ሃምሳ ሺ ብር ይስጡና አምስት ልጆች እንዲያመጣላቸው ቀጭን ትዕዛዝ ይስጣሉ። ውጪያቸውን ከኤርትራዊያንና ተጋሩ በሚያስከፍሉት ያጣጣሉ። የሚገረመው እንደኔ አካል ጉዳተኞች አንድ ዓይን የሌላቸው ሁላ አሉ። ከእነርሱ የሚጠበቅ አምስት ልጆች ማቅርብ እንጂ ለውትድርና ብቁ ናቸው አይደለም የሚለውን የሚመለከተው አካል ብቻ ይለያቸዋል።
በጥንታዊ ባርያ ንግድ የቆዳ ቀለሙ ጥቁር የሆነ ፍርጣማ ጉልበት ያለው፣ ለጉልበት ሥራ ብቁ የሆነውን ነው ለሽያጭ የሚቀርበው። በሰባተኛው ንጉሥ ግን ጥቁር የለ፣ ቀይ የለ፣ አካል ጉዳተኛ ይሁን ህጻን ለውጥ የለውም። ብቻ ለሥልጣኑ ዕድሜ ማራዝሚያ ማገዶ ሆኖ የሚማገድ ትውልድ ይታፈሳል። ይሸጣል ይለወጣል። ደላላው ይሸጣል። አንዳንዱ ደግሞ እንደ ጓደኛዬ ከፍሎ እራሱን ይገዛል። ቤተስብም ልጆቹን መልሶ ይገዛል። ትግራይ አፈሳ አለ እያለ ሲበጠርቅ የነበረ ሁላ አሁን በመዲናችንና በመላ አገሪቱ ያለውን አፈሳ ግን ትንፍሽ የሚል የለም።
"አንድ ሚሊዩን ወጣት አስልፈን፣ የአገሪቱን ሜጋ ፕሮጄክት አቁመን በአሥር ቢልዩን ዶላር መድበን እንዋጋለን" ያለው ጠቅላዩ ቃሉን በተግባር እየፈጽመ ነው።
"የገደለው ባልሽ የሞተው ወንድምሽ
ሀዝንሽ ቅጥ አጣ ከቤት አለውጣ።"
የተባለው ለዛሬም ይሥራል። ወጣት ለአገዛዙ ሹማምንት የገቢ ምንጭ ለአገዛዙ ሥልጣን ማክርሚያ ማገዶ ሆነዋል።
ወላድ ሆይ ጽናቱን ይስጥሽ!👂🤘
(©Nimoona Bortolaa)
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
📌 t.me/Fastsinfo99
🌴 🌴 🌴
Telegram
𝐅𝐢𝐧𝐟𝐢𝐧𝐧𝐞𝐞 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬
✅|| 𝐘𝐀𝐀𝐃𝐀 ykn komii yoo qabaattan nuuf barreessaa.
✅|| ማንኛውም አስተያየት ወይም ቅሬታ ካለዎት ይፃፉልን
✅|| write to us if you have any comments or complaints.
👀 @Fastmereja_Bot 👀

September 2, 2026 880 1