የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል ክፍለጦር ለተማሪዎች የትምህርት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል ክፍለጦር ለተማሪዎች የትምህርት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜ 04 ቀን 2018 ዓ.ም

ድጋፉ የተደረገው በሰሜን ሸዋ ዞን ጫንጮ ከተማ ቀበሌ 01 ሲሆን በቦታው በመገኘት ድጋፉን ለሱሉልታ ወረዳ የአቅመ -ደካማ ቤተሰብ ህፃናት ተማሪዎች ያስረከቡት የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል ኮማንዶ ክፍለጦር አዛዥ ኮሎኔል ግርማ ደምለው ናቸው።

ከራስ በፊት ለህዝብ እና ለሃገር በሚለው እሴታችን መሰረት ሰራዊታችን ለሀገሩ ሰላም ከሚከፍለው የህይወት መስዋዕትነት በተጨማሪ በሀገሩ ልማት ላይ በመሳተፍ እና ወገኖቹን በማገዝ ህዝባዊነቱን እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል።

የሪፐብሊኩ ጥበቃ ክፍለጦር አመራርና አባላት ከደመወዛቸው ላይ በመቀነስ ለነገ ሀገር ተረካቢ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል።

ከሁለት መቶ ሺ ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለ167 ታማሪዎች የደብተር መያዣ ቦርሳ በመለገስ እና መዓድ ማጋራት መደረጉን የገለፁት ዋና አዛዡ በቀጣይም ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ያሉ ሲሆን ለሀገራችን የዕድገት ጉዞ እንቅፋት የሚሆኑ ፀረ-ሰላም ሃይሎችን በመደምሰስ የህዝባችንን ሰላም ከማረጋገጥ ጎን ለጎንም በልማትም ተሳታፊ ሆነን እንቀጥላለን ብለዋል።

የሱሉልታ ወረዳ አስተዳደር አቶ ሲሳይ በሻዳ በበኩላቸው የመከላከያ ሰራዊታችን የሀገሩን ሰላም ለማረጋገጥ ከጠላት ጋር አንገት ለአንገት ተናንቆ የማትተካ ህይወቱን እየከፈለ ይገኛል ለዚህም ትልቅ ክብረ አለን ሲሉ ከምስጋና ጋር ገልፀዋል። ዘገባው የመቅደስ ጌታሁን ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
❤15👍12🔥1🥰1
September 9, 2026 3K