🔶አሻም ቲቪ በፍርድ ቤት ክርክር ተሸነፈ
አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ የሰራተኞቹን የ4 ወር ያልተከፈለ ደሞዝ ሳይከፍል ተቋሙን መዝጋቱን ተከትሎ፣ የቀድሞ ሰራተኞቹ ባቀረቡት ክስ ፍርድ ቤት የሰራተኞቹን አሸናፊነት የሚገልፅ ውሳኔ አስተላልፏል።
ሰራተኞቹ መብታቸውን ለማስከበር ላለፉት 6 ወራት በፍርድ ቤት በጽናት ሲከራከሩ የቆዩ ሲሆን፣ ፍርድ ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረትም ተቋሙ ለሠራተኞቹ ያልከፈላቸውን ደሞዝ እና ተያያዥ ጥቅማጥቅሞች እንዲከፍል የሚያስገድድ ውሳኔ ወስኗል።
ይህ ውሳኔ በሚዲያ ዘርፉ ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎችን የሰራተኞችን መብትና ጥቅም ለማስከበር ትልቅ ማሳያ የሚሆን ሲሆን፣ ተቋማት የፋይናንስ ፈተና ቢገጥማቸው እንኳ የህግና የውል ግዴታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ግልፅ መልእክት አስተላልፏል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

20
7August 17, 2026 2K 9