Event Addis Media: post #6973 — TG.ME

🔶ዓለም አቀፉ የወጣቶች ቀን በድምቀት ተከበረ

​"የወጣቶች ቀን፣ የበጎ ፈቃደኝነት እና የተለያዩ  እድሎች” በሚል መሪ ቃል በብሪቲሽ ካውንስል አዳራሽ የተዘጋጀው የ2026 ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።

​በ'ስዊት ላይፍ ፎር ኦል' (Sweet Life For All) ዋና አዘጋጅነት፣ ከብሪቲሽ ካውንስል፣ ከኢትዮጵያ የብሪታንያ ኤምባሲ እና ከቲኤች group (TH Group) ጋር በመተባበር በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ታዳጊ ተማሪዎች  ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል።

መድረኩ ወጣቶች የሚማሩበት፣ የሚወያዩበት፣ ትስስር የሚፈጥሩበት እና ተስፋ የሚያንፁበት አጋጣሚን ፈጥሯል።

​በበዓሉ አከባበር ላይ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ወጣቶች ስፖርት ቢሮ፣ ከብሪቲሽ ካውንስል እንዲሁም ከብሪቲሽ ኤምባሲ የተወከሉ እንግዶች እንዲሁም የሲቪል ማህበራት መሪዎች የተገኙ ሲሆን፣ የወጣቶች ድምፅ የፕሮግራሙ ዋና ማዕከል ሆኖ ውሏል።

​በወጣቶች የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት ዙሪያ ያተኮረ አሳታፊ እና አበረታች ውይይት ተካሂዷል።በስደት እና ተዛማጅ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ገለፃ ተደርጓል።

​በወጣቶች የተዘጋጁ ኤግዚቢሽኖች የቀረቡ ሲሆን፣ አወንታዊ የሥራ ትስስሮችም ተፈጥረዋል።​ይህ መድረክ ወጣቶች ማህበረሰባቸውን የማገልገል እና ለማህበራዊ ችግሮች መፍትሔ የማፍለቅ ከፍተኛ አቅም እንዳላቸው በተግባር ያሳየ እንደነበር ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😁8❤2
August 12, 2026 3.2K 7