“ቢትኮይን የማንም ዕዳ (IOU) አይደለም!” — ኬትሊን ሎንግ
የዎል ስትሪት የቀድሞ አንጋፋና የ Custodia Bank መስራች ኬትሊን ሎንግ ስለ ቢትኮይን እና ስለ ባህላዊው የፋይናንስ ሥርዓት የተናገሩት ጥልቅ ሀሳብ፦
📉 "በአሁኑ ወቅት የቢትኮይን ዋጋ ከፍተኛ መዋዠቅ (Volatility) ያሳያል። ነገር ግን እንደ ሥርዓት በጣም ጠንካራና አስተማማኝ ነው፤ ምክንያቱም በውስጡ ምንም ዓይነት ዕዳ (Debt) የለም።"
"ቢትኮይን የማንም 'ዕዳ አለብኝ' (IOU) ደረሰኝ አይደለም፤ በአንጻሩ እያንዳንዱ የዶላር ኖት የተስፋ ደረሰኝ (IOU) ነው።"
🛡️"የለፋሁበትን የድካሜን ፍሬ ማንም ሊያጭበረብረውና ሊያዛባው በማይችለው ታማኝ መዝገብ (Honest Ledger) ላይ ማስቀመጥ እመርጣለሁ።"
የፊያት ገንዘብ (እንደ ዶላር ያሉ) በማዕከላዊ ባንኮች የብድርና የዕዳ ሥርዓት ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ ቢትኮይን ግን በብሎክቼይን ቴክኖሎጂ አማካኝነት በማንም የማይቀየር፣ የማይታለልና ያለ ምንም ዕዳ የሚሰራ ነፃ የፋይናንስ መዝገብ ነው።
@ethiocrypto52






