ፍ ር ሃ ት
═✦═
✍ አበራ ለማ
'
ያ መረቡ ልቤ -
ረገበ እምቢ አለ
አንድ ራሱን ማስገር -
አቃተው ዋለለ፤
ፍርሃቴ ስጋቴ -
በላዬ ነገሠ
ውስጥ አንዠቴን ምሶ -
ቤቴን አጣረሰ፤
ግና ምነው ፈራሁ -
ወኔዬ ባዘቀ
በፍርሃት ነቅዤ -
ነፍሴ ተጨነቀ?
እድሜ እንደ ብል ሆኖ -
ህይወት ካነተበ
ፍርሃት ንጉሥ ሆኖ -
አገር ካስደመመ
እናንተም እንደኔው -
ፍርሃት ካባዣችሁ
ጠመንዣው፣ ዣንጥላው -
ውሻው ለምናችሁ?
═════════
🗓 1982 ዓ.ም.
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/Ethiobooks

2
2September 4, 2026 418 3