" ፍጥረት አይለም ሊያደርገው ሊያስበው እንኳን የማይችለው ግብ " በማለት ጣሊያናዊው የስፖርት ጋዜጠኛ እና የእግር ኳስ ተንታኙ ጋብርኤል ማርኮቲ ግቧን ይገልፃታል...
የስኮትላንዱ ሀምፕደን ፓርክ (ሬንጀርስ) የእንግሊዙን ማንችስተር ዩናይትድ በ Away_Goal ያሸነፈውን የጀርመኑን ባየር_ሊቨርኩሰንን እና የ ምንግዜም ተቀናቃኙን ባርሴሎናን በአሳማኝ ሁኔታ አሸነፎ የመጣውን ሪያል_ማድሪድን ለፍፃሜ ጨዋታ አፋጧል
ገና ጨዋታው በተጀመረ በ8 ኛው ደቂቃ ስፔናዊው ጉል አዳኝ ራውል_ጎንዛሌዝ ከግራ ክንፍ ከ ሮቤርቶ ካርሎስ የተሰነጠቀለትን ኳስ በቀላሉ ወደ ጎል ቀየራት
➬ ማድሪድ 1-0 ሊቨርኩሰን
ጨዋታው ቀጥሏል
በ 13ኛው ደቂቃ በክንፍ በኩል ፈረንሳዊው ክላውድ_ማኬሌሌ ሚሸል_ባላክን በመጥለፉ ለባየር ሊቨርኩሰን የተሰጠውን ቅጣት ምት በርናንድ ሽናይደር ወደ ግብ ሲያሻማው ብራዚላዊው ሉሲዮ በግንባሩ በመግጨት ግብ አስቆጥሮ ክለቡን አቻ አደረገ
ጨዋታው እየተጋጋለ ነው
ሊቨርኩሰን በ #ብራዲች #ዚኮቪች እና ባላክ ተደጋጋሚ የጎል ሙከራዎችን አደረጉ
45ኛው_ደቂቃ
ከመሀል ሜዳ አካባቢ ሳንቲያጎ_ሶላሪ በግራ ክፍን በኩል ለነበረው ሮቤርቶ_ካርሎስ ኳሳን አቀበለ ካርሎስም የተሰጠውን ኳስ ወደ 16ከ 50 አሻገረው
በዚህ ቅፅበት ፈረንሳዊው ታዕምረኛ #ዚነዲን_ያዚድ_ዚዳን የተሻገረውን ኳስ ማንም ባላሰበው እና ባልጠበቀው መልኩ በግራ እግሩ ቮሊ በመምታት በ ጆርጌ_በት መረብ ላይ አሳረፈው...
ሪያል ማድሪድም ለ 9 ጊዜ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ
ጣሊያናዊው የእግር ኳስ ተንታኝ እና ጋዜጠኛ #ገብርዔል_ማርኮቲ ጎሏን "ፍጥረት አይደለም ሊያደርገው ሊያስበው እንኳን የማይችል ጎል" በሚል ቃል ገልፇታል
እኔ ባንተ ምክንያት በእግር ኳስ ፍቅር እብድ እንድሆን ዘንድ እንኳን ተወለድክ

June 23, 2024 712 1