የጀርመን ልማት ባንክ (KfW) ለደቡብ አፍሪካ ቅናሽ ያለው 200 ሚሊየን ዩሮ ብድር ሊሰጥ ነው፡፡ ገንዘቡ… — Development Bank of Ethiopia (DBE) — TG.ME

የጀርመን ልማት ባንክ (KfW) ለደቡብ አፍሪካ ቅናሽ ያለው 200 ሚሊየን ዩሮ ብድር ሊሰጥ ነው፡፡

ገንዘቡ የደቡብ አፍሪካን የሜትሮ ንግድ አገልግሎቶች ማሻሻያ ፕሮግራም (MTSR) ለመደገፍ የሚውል ነው።

ፕሮግራሙ መሠረታዊ ንግድ ነክ አገልግሎቶችን ማለትም የኤሌክትሪክ፣ የውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን፣ እንዲሁም የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደርን ለማሻሻልና ለማደስ የተነደፈ ነው።

በስምንት የሜትሮፖሊታን ማዘጋጃ ቤቶች የሚደረገው ይህ ማሻሻያ ከ22 ሚሊየን በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።

የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ (AFD) ለዚሁ ፕሮግራም ተጨማሪ 100 ሚሊየን ዩሮ የሚያበድር ሲሆን፣ በዚህም ደቡብ አፍሪካ ከሁለቱ ተቋማት በድምሩ 300 ሚሊየን ዩሮ (ከ5.6 ቢሊዮን የደቡብ አፍሪካ ራንድ ጋር እኩል የሆነ) ቅናሽ ያለው ብድር የምታገኝ ይሆናል።

መረጃው የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ግምጃ ቤት ነው፡፡

#DBE #KfW #AfD
❤5👍3
September 4, 2026 1.6K