በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከፍተኛ የፋይናንስ ድጋፍ ከተደረገላቸው ግዙፍ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አንዱ ትረስት… — Development Bank of Ethiopia (DBE) — TG.ME

በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከፍተኛ የፋይናንስ ድጋፍ ከተደረገላቸው ግዙፍ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አንዱ ትረስት ፋርማሲዩቲካልስ ማኑፋክቸሪንግ (Trust Pharmaceuticals Manufacturing) ነው፡፡

ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ ለቆዳ ሕክምና አገልግሎት የሚውሉ ቅባቶችንና የመድኃኒት ዓይነቶችን (Dermatological Products) በከፍተኛ ጥራት በማምረት በሀገር አቀፍ ደረጃ ቀዳሚው የዘርፉ አምራች ነው፡፡

ፋብሪካው ወደ ምርት ሲገባ፣ በዘርፉ ከውጭ የሚገቡ የቆዳ ሕክምና መድኃኒቶችን እስከ 15 በመቶ የሚደርሰውን አቅርቦት በሀገር ውስጥ ምርት የሚተካ ይሆናል፡፡

ይህም በየዓመቱ ለቆዳ ሕክምና መድኃኒቶች ግዥ ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከመታደጉ ባሻገር፣ የሀገር ውስጥ የመድኃኒት ዋጋ መረጋጋትን ያረጋግጣል፡፡

በተጨማሪም ፋብሪካው የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ከመሸፈን አልፎ ምርቶቹን ለጎረቤት ሀገራትና ለመላው የአፍሪካ ገበያ የመላክ (Export) አቅም ይዞ የተነሳ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከዚህ ቀደም መሰል ስትራቴጂካዊ የመድኃኒት ፋብሪካዎችን ፋይናንስ ያደረገ ሲሆን፣ የሀገሪቱን የጤና ዘርፍ ጥገኝነት በመቀነስ እና የመድኃኒት አቅርቦት ክፍተትን በሂደት በማጥበብ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እያበረከተ ይገኛል
❤3👏1
September 2, 2026 1.9K 1