ሴት ልጅ ፍቅርን የምትገልጸው እና የምትጠብቀው በቀኑ ውስጥ በየሰዓቱ በሚደወል ስልክ፣ በሚያማምሩ ቃላት እና… — Bemnet Library — TG.ME

ሴት ልጅ ፍቅርን የምትገልጸው እና የምትጠብቀው በቀኑ ውስጥ በየሰዓቱ በሚደወል ስልክ፣ በሚያማምሩ ቃላት እና በስሜታዊ ቅርበት ነው። ወንድ ልጅ ግን ፍቅሩን የሚገልጸው ጠዋት ወጥቶ በማታ ላንቺና ለቤቱ በመልፋት፣ ከማንኛውም ችግር አንቺን ለመታደግ ራሱን አሳልፎ በመስጠት እና ጥበቃ በማድረግ ነው።

ስለዚህ ሴቶች ወንድ ልጅ ፍቅሩን ልክ እንደ ሴት እንዲገልጽላችሁ አትጠብቁ። በቀን ውስጥ 20 ጊዜ እወድሻለሁ ባይልሽም እንኳ፣ ላንቺ ሲል የሚከፍለውን መስዋዕትነት እና ለህይወታችሁ የሚያደርገውን ድካም እንደ እውነተኛ የፍቅር ቋንቋው ተረጂለት።

📕 ርዕስ እንደ ሴት ሁኚ፤ እንደ ወንድ አስቢ
✍️ ደራሲ ስቲቭ ሃርቪ

📚 @Bemnet_Library
❤140👍23💯5🤗5🔥3👏3🙏3✍2❤‍🔥2😱2🫡1
September 1, 2026 4.8K 4 57