ዛፍ ቢቆረጥ ደግሞ እንዲያቆጠቁጥ ወደ ነበረበት ልምላሜ እንዲለወጥ ቅርንጫፉም እንዲያድግ ተስፋ አለው የውኃው ሽታ ስሩን ሲያገኘዉ የሰውም ህይወት እንዲህ ነው በመንፈስህ ነው የሚለመልመው የመንፈስህ ውኃ ሲያገኘው ከሞት ወደ ህይወት ፈጥኖ የሚመለሰው ደርቀው የነበሩ አጥንቶች በሙሉ ታላቅ ሰራዊት ሆነዋል መንፈስህን ሲሞሉ ተስፋ አለው መንፈስህ ሲያገኘው/4* 1. ውስጥን ዘልቆ አልፎ ነፍስን ይመርምር ከፍ እያለ ይውጣ ልኬቱ ይጨምር የህይወት ውኃ ይፍለቅ ይትረፍና ይለምልም በረሀው ዛሬም እንደገና ምድረበዳው እንዲለመልም አለቱም ውኃን እንዲያፈልቅ የተጠማ በጥም እንዳያልቅ የመንፈስህ ዝናብ ይለቀቅ እሳት ጭራሮን እንዲያቃጥል ደግሞም ውኃውን እንዲያፈላ የረከሰውን ሁሉ ሊቀድስ የባለ ኅምሳው እሳት በህዝብህ ላይ ይፍሰስ 2. ህይወት ለከበዳት ላቃታት ብርቱ ሰልፍ እሳት ለናፈቃት ሀዘኗል ለማለፍ ደመናውን እያየች የምትጮኸውን ነፍስ መንፈስህን ሳትሞላት ከዚህ አትመልስ ምድረበዳው እንዲለመልም አለቱም ውኃን እንዲያፈልቅ የተጠማ በጥም እንዳያልቅ የመንፈስህ ዝናብ ይለቀቅ እሳት ጭራሮን እንዲያቃጥል ደግሞም ውኃውን እንዲያፈላ የረከሰውን ሁሉ ሊቀድስ የባለ ኅምሳው እሳት በህዝብህ ላይ ይፍሰስ ደርቀው የነበሩ አጥንቶች በሙሉ ታላቅ ሰራዊት ሆነዋል መንፈስህን ሲሞሉ ተስፋ አለው መንፈስህ ሲያገኘው/4*
26
4
3