ከምለው በላይ ስራህ ገርሞኛል ከአሳቤም በላይ ለእኔ ሆኖብኛል ሌላ እነዲልመኝ በአንተ ተይዤ ኖራለሁ በቃ ፍቅርህን ብዬ ውዴ አንተን ብዬ ምስጋናዬ ፊትህ ይቅረብልኝ አምልኮዬ ማደርያህ ይድረስ የምስጋና የእልልታ ዜማዬ ያርግ ፊትህ ይድረስህ ጌታዬ 1. ከአንደበቴ በላይ የሆነው ስራህ ከቃላትም ከቁጥር አለፈ በረከትህ ፀጋህ መጎብኘትህ ለትውልዴ ለዘሬም ተረፈ ፍቅርህን ምህረትህን እያሰብኩ በላይ በላይ ምስጋናን ልጨምር አምልኮዬን ይዤ ልቅረብ እና በደስታ በፊትህ ልዘምር ምስጋናዬ... 2. ስገዛልህ በፊትህ ዝቅ ብዬ ራሴንም ለአንተ ሳዋርድ ክብሬንም ጥዬልህ በፊትህ ጎንበስህ ብዬ ለክብርህ ስሰግድ መዋረዴ ደስ ያስሰኝህ እና እንደገና ታቆመኛለህ ከአንዱ ክብር ወደሌላ ክብር በመንፈስ ታሻግረኛለህ ይልቁን ጠዋት እና ማታ እየበዛ ይሄዳል ምስጋናዬ ዘውትር ይጨምራል ላመስግንህ ኢየሱስ በአማረ ዜማ በእልልታ ላክብርህ ውድዬ በአምልኮ ዜማ በደስታ 3. ምድረ በዳ በሆነው ህይወቴ ምንም ነገር በአልነበረበት የእኔ ኢየሱስ ይችላል አልኩ እና በምሕረቱ ተማመንኩበት ምንም የሰናፍጭ ቅንጣት ባትሆንም ትንሿ እምነቴ በረከቱን አትረፈረፈልኝ በምስጋና አቆመኝ አባቴ
17August 3, 2025 2.7K 1 26