የኔ አምልኮ ይለያል የኔ አምልኮ *4 በጨው የተቀመመ በእሳት የተቃጠለ ፈጥኖ ወደ ላይ ሚያርግ እሳት ይዞ ሚመለስ ተወራርጃለው በክንዱ እንደማላፍርበት አምኜ ሰምቶ በእሳት የሚመልስ እሱ አምላክ ይሆናል ብዬ እረ እኔስ ቀናው ጨካኞች ክብራችውን ጥለው እረ እኔስ ቀናው ሲያጥኑ ለማይናገረው ሲነጋገሩ ሰምቼ ሲፎካከሩት ሀይሉን አሳየ በለጠ የኔ አምላክ በእሳት ተነሳ በሀይሉ ሀሰትን ፅጥ ሊያሰኝ አፈረ የታመነ ሁሉ አምላኬ ሲገለጥ በክብሩ ሀይሉን አሳየ ደረሰ ክብሩ በአደባባይ ሀይሉን አሳየ ከሁሉ ከጣኦታት በላይ ዲያጎን ወደቀ በፊቱ መቆም አቅቶት ታየ በዙፋኑ ልዑል ቃሉን ሰጠ ተራሮች ዝቅ አሉ ምድር ተናወጠ ማይገዛም አይኖርም ለሱ ክብር ማይሰጥ ሲገለጥ በክብሩ የማይንቀጠቀጥ
21
3
2August 1, 2025 2.5K 27