🔴All⚡️Exit⚡️Question⚡️(AEQ): post #11295 — TG.ME

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 ዓ.ም የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ውጤቶች ይፋ ተደርገዋል፡፡ በክልሉ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን፤ ድጋፍ ለሚሹ ደግሞ 48 የማለፊያ ነጥብ እንደሆነ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አብዮት ደምሴ ገልፀዋል፡፡ በዚህም በክልሉ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 78,203 ተማሪዎች መካከል 47,307 ተማሪዎች (60.4%) የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡   540 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ማሳፍ ሲችሉ፤ 155 ትምህርቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል። በተመሳሳይ በክልሉ የ6ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 126,224 ተማሪዎች መካከል 110,566 ተማሪዎች (63.8%) የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡   የ6ኛ ክፍል ፈተና ያስፈተኑ 476 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ሲያሳልፉ፤ 81 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አላሳለፉም ብለዋል። የ8ኛ ክፍል ውጤት ለማየት 👇 https://se.ministry.et/#/result የ6ኛ ክፍል ውጤት ለማየት 👇 https://se6.ministry.et/#/result    ትምህርታዊ መረጃ™ ✅ ✅ ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ 🔻@AllExitQuestion

August 5, 2026 348