🔴All⚡️Exit⚡️Question⚡️(AEQ): post #11290 — TG.ME

#ቅሬታ #Pharmacy #Exit ትናንት ሰኔ 10/2018 ዓ.ም በተሰጠው የፋርማሲ ትምህርት የመውጫ ፈተና ላይ ስርቆት ተፈፅሟል ሲሉ በርካታ ተፈታኝ ተማሪዎች ቅሬታቸውን እያቀረቡ ነው፡፡ "የፋርማሲ ትምህርት የመውጫ ፈተና አስቀድሞ ተሰርቋል" ያሉት ቅሬታ አቅራቢ ተማሪዎቹ፤ የሚመለከተው የመንግሥት አካል ማብራሪያ እንዲሰጥም ጠይቀዋል። ለፈተናው ዝግጅት ሲያደርጉ ቢቆዩም፣ ኃላፊነት በማይሰማቸው አካላት አማካኝነት ፈተናው ቀድሞ ወጥቶ መሰራጨቱን የሚያሳዩ መረጃዎች እንደደረሷቸው ቅሬታ አቅራቢ ተማሪዎቹ ገልፀዋል። ይህ መሆኑም በከፍተኛ ጥረትና በራሳቸው ልፋት የተፈተኑ ተማሪዎችን ስነ-ልቦና በእጅጉ የጎዳና ፍትሃዊነትን የጎደለው ተግባር መሆኑን ጠቁመዋል። ጉዳዩ በትምህርት ሚኒስቴር፣ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንዲሁም በኢትዮጵያ ፋርማሲስቶች ማኅበር በኩል በአስቸኳይ ታይቶ፣ አስፈላጊው ማጣሪያ እንዲደረግና ተገቢው ምላሽ እንዲሰጣቸው ተፈታኞቹ ጠይቀዋል። ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ከተፈታኝ ተማሪዎች የቀረበውን ይህንን ቅሬታ መነሻ በማድረግ፣ በጉዳዩ ላይ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። ተጨማሪ ማብራሪያ እንዳገኘን የምናደርሳችሁ ይሆናል። 🔴ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ! ✈️ ✈️https://t.me/AllExitQuestion

❤4
June 18, 2026 883 1