🔴All⚡️Exit⚡️Question⚡️(AEQ): post #11276 — TG.ME

የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ቀን ሁለተኛ ዙር የመውጫ ፈተና በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ ** ቢሾፍቱ ፣ ሰኔ 04 ፣ 2018(ኢመዩ) በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በመሰጠት ላይ የሚገኘው የ2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና (Exit Exam) በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ቀን ሁለተኛ ዙር ፈተና በተሳካ እና በተደራጀ ሁኔታ ተከናውኗል። በዚህ ዙር የሎጀስቲክስ እና ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት (Logistics and Supply Chain Management) መርሃ-ግብር ተማሪዎች የመውጫ ፈተናቸውን የወሰዱ ሲሆን፣ የፈተናው አፈፃፀም በዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ በፈተና አስተባባሪዎች እና በሌሎች ተዛማጅ አካላት በተደረገ ሰፊ ቅድመ ዝግጅትና ቅንጅታዊ ሥራ መሠረት በተገቢው ሁኔታ ተፈጽሟል። ተፈታኞች የፈተና አዳራሾቻቸውን እና የተመደቡበትን ክፍል አስቀድመው በማረጋገጥ ወደ ፈተና ማዕከላት የገቡ ሲሆን ፣ የመጀመሪያው ቀን የፈተና ሂደት ያለምንም እክል በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። በቀጣይ ቀናትም የፈተና ሂደቱ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል በመታገዝ እስከ ሰኔ 12/2018 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል። ለመከላከያ ሰራዊታችን ልህቀት እንተጋለን!        የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ @AllExitQuestion

June 11, 2026 524