የትኛው ዩኒቨርሲቲ እና ምን አይነት Department መግባት እንዳለባችሁ በጥንቃቄ ማሰብ አለባችሁ። ይህን ለማድረግ ደግሞ እነዚህን ነገሮች አስቡባቸው፤
በጣም የሚስባችሁ የትኛው የትምህርት አይነት እንደሆነና ወደፊት ምን መስራት እንደምትፈልጉ ለራሳችሁ ግልጽ ማድረግ።
ለምሳሌ website, mobile apps የመሣሠሉት ላይ መስራት የምትፈልጉ ከሆነ፣ እነዚህን ትምህርት የሚሰጡ ዩኒቨርሲቲዎችን መምረጥ ትችላላችሁ ፤ like Software, computer science ,it department ያላቸውን።
ዩኒቨርሲቲው ጥሩ ስም ካለውና ጥራት ያለው ትምህርት የሚሰጥ ከሆነ አሪፍ ነው። በተለይ ደግሞ እናንተ የምትፈልጉት department ምን ያህል ጥራት እንዳለው ማረጋገጥ አለባችሁ።
እንደ አዲስ አበባ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር ያሉ ትላልቅ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተፈላጊ የሆኑ Departመንቶች ላይ ለመግባት ፍክክር አለ። ምክንያቱም ብዙ ጎበዝ ተማሪዎች ከ እነዚ ዩኒቨርቲዎች ስለሚኖሩ እና አብረዋችሁ ስለሚወዳደሩ ውጤታችሁ(GPA) ከፍ ያለ መሆን አለበት።
ስለዚህ የትምህርት ፍላጎታችሁን ብቻ ሳይሆን ውጤታችሁንም እና አቅማችሁንም እያያችሁ የሚመጥናችሁን ዩኒቨርሲቲ መምረጥ አለባችሁ።
ለምሳሌ Adiss Ababa ላይ Software ለመግባት Gpa ከ 3.97 ጀምሮ መስራት ሊጠበቅባችሁ ይችላል፤ እንደ Debre brihan diredawa የመሣሠሉት ደግሞ ከ 3.5፣ 3.7 ጀምሮ ሰርታችሁ መግባት ትችላላችሁ።
ይሄ ብዙ ተማሪዎች የሚሸወዱበት ነው በትኩረት በደንብ አስቡበት፤ አቅማችሁን እወቁ!
...ሌሎች የሰላም ሁኔታ የመሣሠሉት እንዳሉ ሆነው እነዚህን ነገሮች በማሰብ ምርጫ አድረጉ።
JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN


