የ-Anthropic ዋና ስራ አስፈፃሚ Dario Amodei በሚቀጥሉት ከ5 እስከ 10 ዓመታት ውስጥ አብዛኞቹን የሰው ልጆች በሽታዎች በ-AI ማዳን እንደሚቻል ገለፁDario Amodei ኩባንያቸው Anthropic በስነ-ህይወት (Biology) እና በህክምና ዘርፍ ላይ የሚያደርገውን ምርምር በከፍተኛ ፍጥነት እያሳደገ እንደሚገኝ ያስታወቁ ሲሆን በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ የመነሻ ፍንጮችን (Early glimmers) እንዲሁም በቀጣዮቹ ዓመታት ውስጥ አስደናቂ ውጤቶችን ለማሳየት እንዳቀዱ ተናግረዋል። በህክምናው ዘርፍ ላይ ለሚደረገው ፈጣን እድገት ያላቸውን ልዩ ትኩረት ሲያስረዱም አባታቸውን በ-Hepatitis C ያጡት 95% ታካሚዎችን ማዳን የሚችለው Sofosbuvir የተሰኘው መድኃኒት ይፋ ከመደረጉ ጥቂት ዓመታት ቀደም ብሎ እንደነበር ገልጸዋል።አክለውም Anthropic በተግባር ተጨባጭ የህክምና ውጤት ሲያመጣ መላው ዓለም በከፍተኛ ድምፅ እንዲሰማው እንደሚያደርጉና የህዝብን አመኔታ ማግኘት የሚቻለው በባዶ ማስታወቂያ ሳይሆን በሽታዎችን በትክክል በማዳን ብቻ እንደሆነ አስረድተዋል። @AddisIntelt.me/addisintel/15234TranslateAugust 18, 2026 51