የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ ሰይፈ ደርቤ ''የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ'' በተሰኘው ሀገራዊ የምክክር መድረክ ላይ እንዳቀረቡት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከምስረታው ባልተናነሰ የለውጡ መንግሥት በዘረፉና በተቋሙ ባደረገው ሪፎርም ምክንያት ዳግም ተወልዷል ማለት እንደሚቻል ገልጸዋል።
የተከናወነው የእሳቤ፣ የህግና አደረጃጀት እንዲሁም የአሰራር ሪፎርም፤ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን በአፍሪካ አስተማማኝና ተጽዕኖ ፈጣሪ የዜና ምንጭ በመሆን ብሄራዊ ጥቅምን ማስጠበቅና ብሄራዊ መግባባት መፍጠር የሚያስችል አቅም እንዲላበስ አስችሎታል። ተቋሙ ተደራሽነቱን በማስፋት፣ በቴክኖሎጂ ተደራጅቶ፣ ከኢትዮጵያ ተሻግሮ የአፍሪካ ድምጽ በመሆን የወል ትርክትን እየገነባ ይገኛል።
#PMOEthiopia























