ክፍል_ስምንት ለአድስ ተመራቂዎች አዲስ ተመራቂ ሆነን ሥራ ዓለም ስንቀላቀል ትልቁ ፈተና ምን እንደሆነ… — ABI NOVA♾️ — TG.ME

#ክፍል_ስምንት ለአድስ ተመራቂዎች አዲስ ተመራቂ ሆነን ሥራ ዓለም ስንቀላቀል ትልቁ ፈተና ምን እንደሆነ አውቀዋለሁ። እኔም ራሴ አልፌበታለሁ። በአንድ በኩል የዕለት ኑሮን ለመደገፍና ራስን ለመቻል ፈጣን ገቢ ያስፈልጋል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ሕይወትን የሚቀይር ትልቅ ነገር ለመገንባት ጊዜና ትኩረት ይፈልጋል። ሁለቱን በአንድ ላይ ይዞ መጓዝ ቀላል እንዳልሆነ በደንብ አይቼዋለሁ። ከተሞክሮዬ የተማርኩት ቁልፍ እውነት ግን ይሄ ነው፦ አንደኛ ያለን ጉልበት ትልቁ ካፒታላችን ነው፦ አሁን ያለን ዕድሜና ጉልበት ተመልሶ አይመጣም። ዛሬ በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ነገ የምንቆጭበት ባዶ ድካም ሆኖ ያልፋል። ሁለተኛ ቀኑ ለህልውና፣ ምሽቱ ለነገው ማንነታችን፦ በቀን ያለንን ሥራ ሰርተን የዕለት ፍላጎታችንን መሸፈን ግድ ነው። ማታ ግን ወደ ቤት ስንመለስ ለእውነተኛው ራዕያችን የምንሰጠው ጊዜ ሊኖረን ይገባል። ስራ ውለን ስንመለስ መድከማችን አይቀርም፤ ግን ደግሞ ድካማችን ትልቅ ዋጋ አለው፦ ቀኑን ሙሉ ስንለፋ ውለን ምሽት ላይ ማንበብ፣ አዲስ ክህሎት መማር ወይም የግል ሥራ ላይ መቀመጥ አድካሚ ነው፤ አንዳንዴም ሰውነት ዝሎ ተስፋ ሊያስቆርጥ ይችላል። ግን ያንን ድካም ወደፊት ለሚጠብቀን ነፃነት የምንከፍለው ኢንቨስትመንት አድርገን ካላየነው በስተቀር ምንም ነገር አይቀየርም። አሁን ባለንበት ማንነትና ዕውቀት ረክተን ተቀምጠን የተሻለ ዕድል በራሱ ይመጣል ብለን መጠበቅ አንችልም። ራሳችንን በየቀኑ ካላሳደግን፣ የምንፈልገው ለውጥ በምኞት ብቻ አይመጣም። ጊዜውም ጉልበቱም በእጃችን እያለ ዛሬውኑ በራሳችን ላይ መሥራት መጀመር አለብን። @birhan_nega

September 4, 2026 3