በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የአስኮ አጥቢያ ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 መስተዳድር ሥር በሚገኘው በራሷ ይዞታ ላይ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠች።
በዚህ የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ መርሃ ግብር ላይ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ምክትል ፕሬዝዳንት ፓስተር ለወየሁ ስንሻው፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና በርካታ የምዕመናን ተሳትፈዋል።
በዚህ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ምክትል ፕሬዝዳንት ፓስተር ለወየሁ ስንሻው፣ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን በአሁኑ ወቅት ዘርፈ ብዙ መንፈሳዊና ልማታዊ ስራዎችን እያከናወነች እንደምትገኝ ገልጸው፤ የአስኮ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ በብዙ አቅጣጫዎች እያገለገለች፣ እያደገች ያለች ጠንካራ አጥቢያ መሆኗን በመናገር ጌታ ስላደረገላቸው ቸርነት በማመስገን ደስታቸውን ገልጸዋል።
አያይዘውም በዚህ የማምለኪያ የሕንጻ ግንባታ ላይ ሁሉም ምዕመናን በነቂስ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
የአጥቢያዋ የመሪዎች ጉባኤ ሰብሳቢ የሆኑት ወንድም አገኘው መርሻ ባደረጉት ንግግር፣ ቤተክርስቲያኗ ባለፉት 28 ዓመታት የጉዞ ታሪኳ ውስጥ 5 አጥቢያዎችን ያወጣች ቢሆንም እስካሁን ድረስ ምቹ የሆነ የራሷ የአምልኮ ስፍራ እንዳልነበራት ገልጸዋል።
አሁን ላይ ግን ወደ ታች ቤዝመንቱ 3 የሆነ እና ከላይ ሁለት ፍሎር ያለው የማምለኪያ ህንጻ ለመገንባት ዝግጅት ላይ እንደምትገኝ ገለጸው ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚያወጣና ለቀጣዩ ትውልድ የሚሆን ዘመናዊ ህንጻ ለመገንባት የሚያስችል ምቹ ቦታ ሲሆን ሙሉ ይዞታው በ2 ሺህ ካሬ ሲያርፍ አዲስ የሚሰራው ህንጻ በ500 ካሬ የሚጠጋ መሆኑን በመግለጽ ግንባታው በ 2 ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅ መታቀዱን ይፋ አድርገዋል።
በመጨረሻም በቤተ እምነቱ ም/ፕሬዝዳንት እና በቤተክርስቲያኗ መሪዎች አማካኝነት የመሰረተ ድንጋዩ በይፋ ተቀምጧል።
የአስኮ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ የህንፃ ግንባታ ስራ የቅስቀሳና የማነቃቃት ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወንድም ያሬድ ገብረመድህን በዕለቱ በአምልኮ መርሃግብሩ ላይ ፈንድሬዚንግ ተደርጎ ከሁለት ሚልየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል።
የአስኮ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ከ1000 ሺህ ምዕመናን በላይ ያላት እና የምስራችሁን የወንጌል ቃል የምታደርስ ፣አባላትን እውነተኛ የክርስቶስ ደቀመዝሙር የምታደርግ፣የልጆችን እና የታዳጊዎችን ሁለተናዊ አገልግሎት በመስጠት የምታገለግል እና ድሆችን በማሰብ ትኩረት አድርጋ እንደምትሰራ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ይህንን ፕሮጀክት በገንዘብ ለመደገፍ የሚከተሉትን የባንክ አካውንቶች ተጠቀሙ! ስለምታደርጉት ትብብር ሁሉ እግዚአብሔር ብድራታችሁን በ100 እጥፍ ይክፈል፡-
#ብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ 2600520028337
#ንግድ ባንክ 1000569541852
#አዋሽ 013520974183400
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ
Ethiopian Full Gospel Believers Church - Jesus Christ is the same yesterday, today and forever. Heb 13:8
Ethiopian Full Gospel Believers Church
Jesus Christ the same yesterday, today, and forever. Heb 13:8 The Ethiopian Full Gospel Believers’ Church is a Pentecostal Christian denomination in Ethiopia.

4
1June 8, 2026 638 2