የራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል ከ250 በላይ ለሚሆኑ የጎዳና ተዳዳሪዎች '' የእመርታ ቀንን''… — Addis Ababa Health Bureau / አዲስ አበባ ጤና ቢሮ / AACAHB / — TG.ME

የራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል ከ250 በላይ ለሚሆኑ የጎዳና ተዳዳሪዎች '' የእመርታ ቀንን'' ምክንያት በማድረግ የበጎ አድራጎት ተግባራትን አከናውኗል።

አአ ጤና ቢሮ ጳጉሜ 1 ቀ 2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ስር ከሚገኙ ሆስፒታሎች አንዱ የሆነው የራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል ጳጉሜ1 የእመርታ ቀንን በማስመልከት ከ250 በላይ ለሚሆኑ በጎዳና ለሚገኙ ወገኖች የበጎ አድራጎት ተግባራትን አከናውኗል።

በእለቱ በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ከ 250 በላይ ለሚሆኑ በጎዳና ለሚገኙ ወገኖች የተለያዩ የህክምና አገልግሎቶችን የስኳር ፣ የአይን ፣ የደም ግፊት ፣ የቲቢ ፣ኤች አይቪ ምርመራ ያደረገ ሲሆን ለእነዚሁ ወገኖች የንፅህናቸውን ለመጠበቅ ፀጉር መቁሰጥ ፣ ገላቸውን በማጠብ የአልባሳት እና የማዕድ ማጋራት ድጋፍ አድርጓል።

የራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪጅ አቶ ተሾመ ሁንዴ በሆስፒታሉ ነፃ ህክምናን ጨምሮ በርካታ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ሲሰጡ መቆየታቸውን ገልፀው በዛሬው ዕለትም የዚሁ አካል የሆነውና የእመርታ ቀንን በማስመልከት ነፃ ህክምና አገልግሎት ፣ ማዕድ ማጋራት ፣ ፀጉር መቁረጥ ፣ ገላ ማጠብ እና መሰል የበጎ አድራጎት ስራዎች መተግበራቸውን ተናግረዋል።

ነፃ ህከምና ተደርጎላቸው ቀጣይ ተጨማሪ የህክምና ክትትል ለሚያስፈልጋቸው ሆስፒታሉ አመቱን ሙሉ በነፃ ህክምና የሚያደርግላቸው መሆኑን አቶ ተሾመ አክለው ገልፀዋል።

በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሆስፒታሉ ከ5ሺህ 700 በላይ ለሚሆኑ የተለያዩ ድጋፋ ለሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች በነጻ የተለያዩ ህክምና እንዲያገኙ መደረጉን እና 146 ዩኒት ደም መሰብሰብ አቅመ ደካሞችና አረጋውያን ማቆያ ለሚገኙ ወገኖች ነፃ ህክምና በመሰጠት እና ሌሎች በርካታ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቶች መተግበራቸውን አቶ ተሾመ ተናግረዋል።
❤4
September 6, 2026 1.6K 1