የእመርታ ቀን! በአዲስ አበባ ከተማ እመርታ ያስገኙ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች! በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዓመታት… — Addis Ababa Health Bureau / አዲስ አበባ ጤና ቢሮ / AACAHB / — TG.ME

የእመርታ ቀን!

በአዲስ አበባ ከተማ እመርታ ያስገኙ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች!

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የልማት ስኬቶች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለነዋሪዎች ሰፊ የሥራ እድል በመፍጠር እንዲሁም የኢንቨስትመንት ዘርፉን በማነቃቃት ከፍተኛ ለውጥ ያመጡ ናቸው፡፡

ከተማዋን እንደ አዲስ ከፈጠሩ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች መሀከል የኮሪደር ልማት እንዱና ዋንኛው ነው፡፡ በዚህ ሰፊና ዘመን ተሻጋሪ ስራ ዘመናዊ የመንገድ ግንባታዎች በመግንባትና አስቸጋሪ እና በርካታ አመታት ያስቆጠሩ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት በመለወጥ እንዲሁም ያረጁና የጎሰቆሉ መኖሪያ መንደሮችን በአዲስ በመተካት ብሎም ለንግድ እንቅስቃሴ ምቹ የሆኑ ዘመናዊ ሱቆችንና ማዕከላትን በመገንባት ለነዋሪዎች ምቹ ከባቢን በመፍጠር የተሻለች ውብ ከተማ እንድትሆን ማድረግ ተችሏል፡፡

በከተማዋ የተገነቡ የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች እና የቱሪዝም መዳረሻዎችም ከተማዋን አረንጓዴ ገፅታን በማላበስ ለጤና ምቹ ከተማ እንድትሆን በማድረግ ለቱሪስት ምቹ እና ቀልብ ማረፊያ ከተማ እንድትሆን በማድረግ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ጎብኚዎችን ቁጥር በማሳደግ ለሀገር ኢኮኖሚው ከፍተኛ ሚና ማበርከት ችለዋል፡፡

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ከተማ እምርታን ካመጡ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች መሀከል የስራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሽ ነው፡፡ በዚህ እምርታ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች በማስፋፋት ማዕከላቱን ለስራ አጥ ወጣቶች በማስተላለፍ አምራች እንዲሆኑ ማድረግ የተቸለ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን የከተማዋን ኢኮኖሚ በማሳደግ የከተማ አስተዳደሩ የግል ኢንቨስትመንት በመሳብ ለበርካታ ባለሀብቶች ፍቃድ በመስጠት በግንባታ፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ እንዲሁም በሪል-እስቴት ዘርፎች ሰፊ የሥራ እድሎች እንዲፈጠሩ ምቹ ሁኔታን ተፈጥሯል ፡፡

አዲስ አበባ ያከናወነችው ለትውልድ ተሸጋሪ ሌላኛው ስኬታማ ስራ የትምህርት፣ ጤና እና ማህበራዊ መሰረተ ልማት በማዘመን ትምህርት ቤቶችና የጤና ተቋማትን በማስፋፋት ለትውልድ ተሻጋሪ አንዲሆን የተሰራው አመርቂ ስራ ማሳያ ነው፡፡

በአጠቃላይ አዲስ አበባ ከተማ በተመዘገበው የላቀ ስኬታማ ስራ ከተማዋ ለህፃናት እና ለወጣቶች ምቹ በማድረግ የስፖርት ሜዳና የመጫወቻ ስፍራዎች በመገንባት ለሁሉ የምትመች እና ሁሉን አካታች ከተማ በመሆን አመርቂ እመርታን ማስመዝገብ ችላለች፡፡
❤2
September 6, 2026 693 1