የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በተለያዩ የህክምና ሙያ ዘርፎች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ያስመርቃል።… — Addis Ababa Health Bureau / አዲስ አበባ ጤና ቢሮ / AACAHB / — TG.ME

የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በተለያዩ የህክምና ሙያ ዘርፎች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ያስመርቃል።

አ/አ/ጤና ቢሮ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከህክምና አገልግሎቱ ጎን ለጎን ብቁ የጤና ባለሞያዎችን በማፍራት የድርሻውን እየተወጣ ይገኛል።

በቢሮው ስር ከሚገኙ የጤና ተቋማት እና የህክምና ኮሌጆች መካከል አንዱ የሆነው የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በተለያዩ የህክምና ትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ያስመርቃል።

ኮሌጁ በ9ኛው ዙር ከ250 በላይ ተማሪዎችን በተለያዩ የህክምና ትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ ፣ በማስተርስ ፣ በስፔሻሊቲ እና በሰብ ስፔሻሊቲ ያስመርቃል።

ኮሌጁ በጤናው ዘርፍ ብቁ ባለሞያዎችን በማፍራት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።
❤9👍2👏1
September 5, 2026 1.4K